From Wikipedia, the free encyclopedia
Content deleted Content added
|
Tag:
|
|
||
| Line 1: | Line 1: | ||
|
= ”’አዳብና”’ = |
|||
|
”’አዳብና”’ (English: ”’Adabina”’) በወረሃ መስከረም የሚከበር የልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች የመተጫጫና የጨዋታ ስርዓት ሲሆን ከ800 አመታት በፊት ጀምሮ ሲከውን የነበረ የክስታኔ ጉራጌ ጥንታዊ ባህል ነው። አዳብና በክሰታኔ እና በዶቢ ክስታኔ አካባቢ ለዘመናት በደምቀት ሲከበር የኖረ የጉራጌ መገለጫ ከሆኑት ባህላዊ እሴቶች መሃል አንዱ ነው። የባህሉ መነሻ ምንጭ የክስታኔ ማህበረሰብ ወይም የጎርድና ሴራ ቢሆንም በሌሎች የጉራጌ አካባቢዎችም ጭምር የአዳብና ጫዋታ ይከናውናል። ለዚህም በምሁር አክሊል ፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ እና በመስቃን ጥቂት ስፍራዎች እንደ ክስታኔ ወረዳዎችና ከተሞች እንዳለው ድምቀት ባይሆንም እንደሚከበር ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።<ref name=”:0″>{{Cite book |last=Desta |first=Dr Fekadu |title=የክስታኔ ጉራጌ የጎርደና ሴራ እና ተያያዥ ባህሎች |year=2013 in E.C |publisher=[[Dr. Fekadu Desta]] |edition=1st |location=Addis Ababa, Ethiopia |publication-date=July 2013 in E.C |pages=136-138 |language=amh}}</ref> |

Latest revision as of 23:33, 8 October 2025
አዳብና (English: Adabina) በወረሃ መስከረም የሚከበር የልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች የመተጫጫና የጨዋታ ስርዓት ሲሆን ከ800 አመታት በፊት ጀምሮ ሲከውን የነበረ የክስታኔ ጉራጌ ጥንታዊ ባህል ነው። አዳብና በክሰታኔ እና በዶቢ ክስታኔ አካባቢ ለዘመናት በደምቀት ሲከበር የኖረ የጉራጌ መገለጫ ከሆኑት ባህላዊ እሴቶች መሃል አንዱ ነው። የባህሉ መነሻ ምንጭ የክስታኔ ማህበረሰብ ወይም የጎርድና ሴራ ቢሆንም በሌሎች የጉራጌ አካባቢዎችም ጭምር የአዳብና ጫዋታ ይከናውናል። ለዚህም በምሁር አክሊል ፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ እና በመስቃን ጥቂት ስፍራዎች እንደ ክስታኔ ወረዳዎችና ከተሞች እንዳለው ድምቀት ባይሆንም እንደሚከበር ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።[1]
አዳብና የሚለው ቃል የመጣው ’’አዳምና ሄዋን’’ ከሚለው ቃል ተነስቶ በጊዜ ሂደት’’አዳብና’’ ወይም አዳምና እየተባለ በአጭሩ መጠራቱን የአካባቢው የታሪክ አዋቂዎች ያስረዳሉ። ትርጓሜውም ለአቅመ አዳም ወይም ሄዋን የደርሱ ልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች አቻዎቻቸው የሚመርጡበት ፡ የሚያዩበት ፣ ለትዳር ብቁ መሆናቸው በጭፈራ እና በስፖርታዊ ትእይንቶች የሚያሳዩብት የአደባባይ ጭዋታ ነው።[2]
አዳብና መስቀልን ተከትሎ የሚከብር በአል ሲሆን ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ድረስ በገበያ ቦታዎች ፣ ንግስ ባለባቸው ስፍራዎች እና የህዝብ መሰብስቢያ አደባባዮዎች ይከበራል።[3]
የአዳብና ታሪካዊ አመጣጥ
[edit]
አዳብና በጎርደና ሴራ ከተደነገጉት ህጎች ወስጥ አንዱ ሲሆን ጥንታዊ የጎርድና አባቶች ልጆቻቸው ለአቀመ ሄዋን ሲደርሱ የሚተጫጩበት ፣ የሚተያዩበት ፣ የሚያገባት/ባው ጓደኛ እንዲፈልጉ የሚያግዝ እና በማህበረስቡ ውስጥ አንደነት ፣ ፍቅር ፣ ነጻነት እና ማንነት የሚያሳይ በየአመቱ በመስከረም አጋማሽ ተጀምሮ ጥቅምት አምስት ድረስ እንዲከበር አድርገው ከ800 አመት በፊት የቀረጽት የክስታኔ ጉራጌ ሴራ ነው።[4] [5]
በአዳብና የሚታዩ ትዕይንቶች
[edit]
ልጃገረዶች ቆንጆ ሆነው የሚታዩበት ቀን ሰለሆነ የጉራጌ ባህላዊ ወይም ሽንሽን ልብስ በመልበስ እና ጸጉራቻው በሹሩባ በማሰዋብ አዳብና ጫዋታ ይሳተፋሉ። ወንዶቹም ለትዳር ብቁ መሆናቸው የሚያሳዩበት ቀን በመሆኑ አዲስ ልብሳቸው በመልበስ የአዳብና ጨዋታው ይታደማሉ።
በአዳብና ብዙ አይነት ጨዋታዎች የያዘ ሲሆን ከነዚህም ወስጥ
- ቱባ የጉራጊኛ ጭፈራ ለምሳሌ የቦላላ እና ማንጎሮ ጎሮሮ በተለያዩ ዜማዎች በመታገዝ ይቀርባሉ።
- ሌላው እስፖርታዊ ትዕይንቶች ናቸው – የብትር ዝላ ፣ አጋቲ ዝላይ(የትክሻ ዝላይ) ፣ ሰባ እና ነጆ አራጆ ጨዋታዎች ተጠቃሾች ናቸው።
- ወጣቶች ክብ እየሰሩ ይጨፍራሉ በዚህም ጊዜ አንድ ወንድ ልቡ ላረፈባት ልጃገረድ ሎሚ በመስጠት ፍላጎቱን ይገልጻል። ልጂቷ ሎሚው ከተቀበለችው ወይም ካነሳችው የልጁ ጥያቄ መቀበሏ ምልክት ነው። ከዚያ በኋላ የወንዱ ጓደኞች የልጂቷ ማንነት አጥንተው ለቤተሰብ ያሳውቃሉ። ከዚያም ሰባት ዘር ተቆጥሮ ቤተሰብ አለመሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ሴቷ ቤተሰብ ሽምግልና በመላክ የጋብቻ ስነስርዓቱ ይጀመራል። [6]
- ^ Desta, Dr Fekadu (2013 in E.C). የክስታኔ ጉራጌ የጎርደና ሴራ እና ተያያዥ ባህሎች (in amh) (1st ed.). Addis Ababa, Ethiopia: Dr. Fekadu Desta (published July 2013 in E.C). pp. 136–138. CS1 maint: unrecognized language (link) CS1 maint: year (link)
- ^ ዘምድረ ከብድ, ከተሰፋዬ ገብረየስ (May 1987 E.C). አይመለል (in ISO 639-1 am) (1st ed.). Addis Ababa, Ethiopia: በንግድ ማትሚያ ድርጅት ታተመ. pp. 72–73. CS1 maint: unrecognized language (link) CS1 maint: year (link)
- ^ Fast Mereja, Fast Mereja (September 29, 2025). “የጉራጌ ልጃገረዶች እና የወጣት ወንዶች በዓል የሆነው አዳብና በአዲስ አበባ ሊከበር ነው”. Fast Mereja . pp. 1–2. Retrieved September 22, 2025.
- ^ ሪፖርተር, Ethiopian Reporter (September 22, 2024). “ገፀ ብዙው አዳብና”. Ethiopian Reporter. pp. 1–2. Retrieved September 29, 2025.
- ^ የጎርደና ሸንጎ ዎገትጌ (in amh) (1st ed.). Addis Ababa, Ethiopia: የጎርደና ሸንጎ. April 1986 E.C. p. 19. ; CS1 maint: date and year (link) CS1 maint: unrecognized language (link) CS1 maint: year (link)
- ^ TADESSE ROBELE, WALELIGN (September 30, 2025). CONTINUITY AND CHANGE IN YE- GORDENA SERA SYSTEM OF KISTANE-GURAGE TRADITIONAL LOCAL GOVERNANCE (1st ed.). Addis Ababa, Ethiopia: WALELIGN TADESSE ROBELE (published June 2005). pp. 66–67. ; CS1 maint: year (link)